ቅዳሜ 17 ጃንዋሪ 2015

አድርገህልኛልና

፮ አድርገህልኛልና
አድርገህኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሀለው እልል እልል
ለዓለም ወለዓለም ዓማኑዔል
እገዛልሀለሁ መድኃኔዓለም

ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሁኖ
የችግር አረንቛ ፊቴ ተደቅኖ
እረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈጽሞ አራኽልኝ የልቤን ትካዜ
አዝ…………….
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያየ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻየ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄያለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ
አዝ………….
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ
በቀንም በሌሊትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባሕርይሕ ዕጹብ ላንተ ስራ
አዝ…………..
አምላኬ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባሃል
ለትንቯ ጎጆ በረከት ሰጥተሀል
ድሀ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሰሮየር ሞልቷል ሳይጎድል እንደገና

አዝ………………….

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ