፲፮ እስከመቼ ነው
እስከመቼ ነው የማልለወጠው
ባልተሰበረ ልብ የምመላለሰው
በሰጠኸኝ ፀጋ ድካሜ ተከድኖ
ዓለም ይከበኛል አልቆና አግኖ
ይህን ከንቱ ወጥመድ ጣለው ከxላዬ
ትንሽ ሰው መሆኔን ይወቅ ህሊናዬ
ኣዝ……………
ፀሐይ ስትጠልቅ ከዋክብት ሲረግፉ
ለገናናው ክብርህ ፈቅደው ሲሸነፉ
ለሁለት ሲከፈል ድንጋያማው ዓለት
የኔ ልብ መች ይሆን የሚሸነፍለት
ኣዝ…………
ቃልህን ስሰማ ልቤን ይነካኛል
ፅድቄን አስባለሁ ሀዘን ይሰማኛል
ወዲያው ተመልሸ ሁሉን እረሳለሁ
ለዚህ –ለም ስብከት ልቤን አከፍታለሁ
ኣዝ………..
መኖርን እሻለሁ ልቤ ተለውጦ
አንተን እንዲያከብርህ ከሁሉ አብልጦ
–ልለት
አይሁን ይቅር ይሰበር ከፊትህ
ደንግጨ አንድመለስ ሲገስፀኝ ድምፅህ
ኣዝ…….
ዲ/ቴድሮስ
ዮሴፍ ቁ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ