፮
ውደማደሪያው ገብቸ
ወደማደሪያገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር
በአጸደ መቅደሱም እሰግድለታለሁ
በፊቱ ለመቆም ማልጀ እነሳለሁ (፪)
አዝ……………
በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቸ በፍጹም ደስታ
የከንፈርን ፍሬ ልሰዋ በእልልታ(፪)
አዝ…………..
አስር አውታር ባለው በበገና
በመልዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምተኽኛልና(፪)
አዝ………………..
ለስሙ ልንበርከክ ለአርሱ አንደሚገባ
ስእለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ(፪)
አዝ…………
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቼን ዘርግቸ(፪)
አዝ……………..
ዲ/ወንድወሰን
በቀለ ቁ/፪

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ