፫ ምስጋና አቀርባለሁ
ምስጋና አቀርባለሁ ለሠራዊት ጌታ(፪)
ጠብቆኛልና
ከጧት እስከማታ(፪)
ሰማዩን ለሠራው ምድርን ላነጸት
ውኃውን አስፍፎ እንዲህ ላስዋባት
ለያዕቆብ አምላክ ሁሉን ለሚያደርገው
ጥብቆኛልና ተመስገን ልበለው
አዝ…………
ጭንቅ ብሎኝ ሳለ በስቃይ በህመም
የሚያድነኝ ጠፍቶ ብቻየን ስደክም
አባቴ ሆይ ማረኝ ብየ ስጠራው
በእጁ ለዳሰሰኝ እዘምራለሁ
አዝ…………..
የልመናየን ድምጽ እርሱ ሰምቷልና
ጆሮውን ወደኔ አዘንብሏልና
በክብር ዙፋኑ በሰማይ ለታየው
አልል አልል ብየ እኔም ላመስግነው
መ/ር ዘበነ ለማ ቁ/፩
.jpg)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ