ሰኞ 19 ጃንዋሪ 2015

እስከመቼ ነው

፲፮ እስከመቼ ነው

እስከመቼ ነው የማልለወጠው
ባልተሰበረ ልብ የምመላለሰው

በሰጠኸኝ ፀጋ ድካሜ ተከድኖ
ዓለም ይከበኛል አልቆና አግኖ
ይህን ከንቱ ወጥመድ ጣለው ከxላዬ
ትንሽ ሰው መሆኔን ይወቅ ህሊናዬ
ኣዝ……………
ፀሐይ ስትጠልቅ ከዋክብት ሲረግፉ
ለገናናው ክብርህ ፈቅደው ሲሸነፉ
ለሁለት ሲከፈል ድንጋያማው ዓለት
የኔ ልብ መች ይሆን የሚሸነፍለት
ኣዝ…………
ቃልህን ስሰማ ልቤን ይነካኛል
ፅድቄን አስባለሁ ሀዘን ይሰማኛል
ወዲያው ተመልሸ ሁሉን እረሳለሁ
ለዚህ ለም ስብከት ልቤን አከፍታለሁ
ኣዝ………..
መኖርን እሻለሁ ልቤ ተለውጦ
አንተን እንዲያከብርህ ከሁሉ አብልጦ
ልለት አይሁን ይቅር  ይሰበር ከፊትህ
ደንግጨ አንድመለስ ሲገስፀኝ ድምፅህ
ኣዝ…….
ዲ/ቴድሮስ ዮሴፍ ቁ 

ቅዳሜ 17 ጃንዋሪ 2015

አድርገህልኛልና

፮ አድርገህልኛልና
አድርገህኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሀለው እልል እልል
ለዓለም ወለዓለም ዓማኑዔል
እገዛልሀለሁ መድኃኔዓለም

ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሁኖ
የችግር አረንቛ ፊቴ ተደቅኖ
እረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈጽሞ አራኽልኝ የልቤን ትካዜ
አዝ…………….
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያየ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻየ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄያለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ
አዝ………….
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ
በቀንም በሌሊትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባሕርይሕ ዕጹብ ላንተ ስራ
አዝ…………..
አምላኬ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባሃል
ለትንቯ ጎጆ በረከት ሰጥተሀል
ድሀ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሰሮየር ሞልቷል ሳይጎድል እንደገና

አዝ………………….

ውደማደሪያው ገብቸ

፮ ውደማደሪያው ገብቸ
ወደማደሪያገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር

አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአጸደ መቅደሱም እሰግድለታለሁ
በፊቱ ለመቆም ማልጀ እነሳለሁ (፪)
አዝ……………
በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቸ በፍጹም ደስታ
የከንፈርን ፍሬ ልሰዋ በእልልታ(፪)
አዝ…………..
አስር አውታር ባለው በበገና
በመልዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምተኽኛልና(፪)
አዝ………………..
ለስሙ ልንበርከክ ለአርሱ አንደሚገባ
ስእለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ(፪)
አዝ…………
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቼን ዘርግቸ(፪)
አዝ……………..

ዲ/ወንድወሰን በቀለ ቁ/፪

ወረብ

፬ መመኪያየ አንተ ነህ
መመኪያየ አንተ ነህ(፪) የነፍሴ መዳኛ

ተመልከት ወደኔ አትስጠኝ ለዳኛ


፭ እሳተ ጽሩር
እሳተ ጽሩር ማየ ጠፈሩ (፪)
ደመና መንኮራኮሩ ለመድሀኒዓለም


፰ ይቅርታህ ብዙ ነው
ይቅርታህ ብዙ ነው ለሚጠሩህ ሁሉ(፪)
አድምጠኝ ጌታ ሆይ ተቀበለኝ ፅሎቴን በሙሉ፪) 


፱ ዘበOማያት
ዘበOማያት አቡነ ዘበOማያት
ከዚህ ቤት(፭) ይደር በረከት


፯ ለጌታየ
ለጌታየ ለእግዚአብሔር ስላደረገልኝ ምን እከፍለዋለሁ(፪)ምስጋና ነው እንጅ(፪) ሌላ ምን እላለሁ
ለእመቤቴ ለድንግል ማርያም ስላማለደችንምን እከፍላታለሁ

ምስጋና ነው እንጅ(፪) ሌላ ምን እላለሁ

፲፬ ፀጋ ነP
ፀጋ ነPነ ወሕይወተነ ረከበነ
xይለ መስቀሉ ለእየሱስ ክርስቶስ
xይለ መስቀሉ
ኪያከ እግዚኦ ነአኩተከ ወንሴብሃከ እግዜብሔር

፲፭ አልተወኝም
አልተወኝም ለካስ ጌታ ይወደኛል(፪)

ዛሬም ስበድለው ልጀ ሆይ ይለኛል(፪)


ምስጋና አቀርባለሁ


ምስጋና አቀርባለሁ

ምስጋና አቀርባለሁ ለሠራዊት ጌታ(፪)
ጠብቆኛልና ከጧት እስከማታ(፪)

ሰማዩን ለሠራው ምድርን ላነጸት
ውኃውን አስፍፎ እንዲህ ላስዋባት
ለያዕቆብ አምላክ ሁሉን ለሚያደርገው
ጥብቆኛልና ተመስገን ልበለው
አዝ…………
ጭንቅ ብሎኝ ሳለ በስቃይ በህመም
የሚያድነኝ ጠፍቶ ብቻየን ስደክም
አባቴ ሆይ ማረኝ ብየ ስጠራው
በእጁ ለዳሰሰኝ እዘምራለሁ
አዝ…………..
የልመናየን ድምጽ እርሱ ሰምቷልና
ጆሮውን ወደኔ አዘንብሏልና
በክብር ዙፋኑ በሰማይ ለታየው
አልል አልል ብየ እኔም ላመስግነው

መ/ር ዘበነ ለማ ቁ/፩

እንደቸርንተህ


፪ እንደቸርንተህ
አንደቸርነትህ ኣቤቱ ማረኝ
አንደምህረትህ ይቅርታ ስጠኝ

xጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ
ለዚያች ክፉ ሃጢአት አንዳልሆናት ሎሌ
አኔም አመፃዮን በደሌን ሳውቀው
ፍፁም የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው
አንተን ብቻ በደልሁ ክፉም አደረግሁ
አሁን ይቅር በለኝከፊትህ ወደቅሁ
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን
መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሃን
አሁን ትባርክ ዘንድ ማህበራችንን
ሀገራችንን ጌታ ሆይ ላክልን
መንፈስ ቅዱስን ጰርራሊጦስን
አሁን ትባርክ ዘንድ ፅሎታችንን
ሃይማኖታችን ጌታ ሆይ ላክልን
ቅ/ሚካዔል ቅ/ ገብርዔልን


ስብሐት ለአብ


፩ ስብሐት ለአብ

ስብሐት ለአብ 
ስብሐት ለወልድ
 ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ
ለአብ አና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ከማቅረብ ከቶ ኣንወሰንም
ዛሬም ወደፊትም ደግሞም ለዘላለም
ኣዝ………………
ከዚህ ከማራኪው ከአስጨናቂው ዓለም
የጠራ ይድናል የፈጣሪውን ስም
በውነት ያለሐሰት ያለጥርጥር
ኣዝ………………..
ማንም መድሐኒቱን የሚጠላ የለም
Zችን አንዲያምር ኣንድነታችንም
ሊኖረን ይገባል ፍቅርና ሰላም
ኣዝ………..
ያልከውን ኣስበህ አናንተም ሁላችሁ
ሁለት ሶስት ሁናችሁ በስሜ ካላችሁ
አኔም አገኛለሁ በመካከላችሁ
ኣዝ………….
አቤቱ ኣምላክ ሆይ አንለምንሀለን
አንድትገኝልን በመካከላችን
ይኸው ተገኝተናል ሁለት ሶስት ሆነን
ኣዝ………………..